
መጋቢት 13/2013 ዓ.ም
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ እና የማህበረሰብ አገልግሎት በቡሌ ሆራ ከተማ
በቡሌ ሆራ ከተማ የሚስተዋለውን የመንገድ እጥረት ከመቅረፍ አኳያ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ከዩኒቨርስቲው እስከ የከተማው ዋናው መንገድ (አድማ በታኝ) የሚወስድ 1.5 ኪ.ሜ መንገድ በመስራት ለአገልግሎት ክፍት አደረገ ።
ዩኒቨርሲቲው እየሰራው የሚገኘው መንገድ በርካታ ቁጥር ያለው የማህበረሰብ ክፍል የሚንቀሳቀስበት እና ለረጅም ጊዜ የአስፋልት ንጣፍ ያልነበረው ሲሆን፤ በአካባቢው ለሚኖር ማህበረሰብ እንደ ጎርፍ የመሳሰለ የተፈጥሮ አደጋዎች እና የትራፊክ አደጋ ሲያስከትል ቆይቷል።
ይህንንም ከመቅረፍ አኳያ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ መዋለ ንዋይ በማፍሰስ 1.5 ኪ.ሜ የአስፋልት ንጣፍ አጠናቋል።
ዩኒቨርስቲው ከአስፋልት ንጣፍ መጠናቀቅ በኃላም ሙያዊ ጥናት በማድረግ ማህበረሰቡን ከጎርፍ ተጋላጭነት ለመታደግ የዲች እና የእግረኛ መንገድ በመስራት በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
ዩኒቨርስቲው በተጨማሪም ለከተማው ድምቀት እና ውበት ይሆን ዘንድ የመንገድ ላይ መብራት በመስራት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓት ዘመናዊ የመብራት ፖሎችን ተክሎ አጠናቋል።
ዩኒቨርስቲው ዘርፈ ብዙ የማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራት እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን፤ በቀጣይነትም በማህበረሰብ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ የማህበረሰብ አገልግሎት ለመስጠት በትጋት እየሰራ ይገኛል።
ለላቀ ለዉጥ እንተጋለን!!!