የቡሌ ሆራ ዪኒቨርሲቲ እና የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ፅ/ቤት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

የቡሌ ሆራ ዪኒቨርሲቲ እና የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ፅ/ቤት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

የቡሌ ሆራ ዪኒቨርሲቲ እና የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ፅ/ቤት በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በአዕምሯዊ ንብረት የመብት ጥበቃ፣ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ድጋፍ ማዕከል (TISC) ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ እንዲሁም በተቋማዊ አዕምሯዊ ንብረት ፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ነው በጋራ ለመስራት የተስማሙት፡፡ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በስምምነቱ መሰረት የተለያዩ የምርምር ውጤት ይፋ የሚያደርጉ ድረ-ገፆችን ለመጠቀም የሚረዳ የይለፍ ቃል ያለ ምንም ክፍያ በፅ/ቤቱ በኩል ለማግኘት ያስችለዋል፡