የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለዩኒቨርሲቲው የፋይናንስ አስተዳደር ሠራተኞች እና ባለሙያዎች በፋይናንስ አስተዳደር ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

በስልጠናው ላይ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ቦሩ ህርባዬን ጨምሮ በረካታ ቁጥር ያላቸው የፋይናንስ ባለሙያዎች ተሳተፈዋል::
በስልጠናው በፋይናንስ አስተዳደር፣ በበጀት ምንነት፣ በክፍያ ሁኔታዎች፣ በጥሬ ገንዘብ አጠቃቀም፣ የበጀት መርህ እቅድን ከበጀት ጋር ማስተሳሰር በሚሉ እና በሌሎች ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠናው ተሰጠቷል::
በስልጠናው የፋይናንስ አስተዳደርን ለማዳበር እና ውጤታማ የበጀት አጠቃቀምን ለማሳደግ ከፍተኛ ጠቄሜታ እንዳለው የዩኒቨርሲቲው የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክተሩ በስልጠናው ላይ ገልፀዋል::
በተቋሙ ዉስጥ ለሚከናወኑ የለውጥ ስራዎችና አጠቃላይ የገንዘብ ነክ ጉዳዮች የበጀት አጠቃቀምና ምንነትን ማወቅ አስፈላጊ ስለመሆኑም አንስተዋል::
ለመማር ማስተማር፣ ለተማሪዎች አገልግሎት፣ ለደሞዝ እና ለሌሎች ከተቋሙ የለውጥ ሂደቶች ጋር ለሚከወኑ የፋይናንስ ወጪዎችን ከበጀት መሪ እቅድ ጋር በማስተሳሰር የበጀት ምንነት እና አጠቃቀም መረዳት አስፈላጊ ስለመሆኑም ገልፀዋል::
ለላቀ ለውጥ እንተጋለ!
06/03/2014 ዓ.ም
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ