ጥር 20/2013 ዓ.ም (ቡሆዩ)
ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስተር የተወከለ ልዑካን ቡድን በቡ ሌሆራ ዩንቨርስቲ ጉብኝት አደረጉ።
ልዑካን ቡድኑ የኮረና ቫይረስን እየተከላከሉ መማር ማስተማር ከማስቀጠል አኳያ ዩንቨርስቲው ያለበትን ሁኔታ እየገመገሙ ሲሆን፤ላይብረሪ፣የተማሪወች ምግብ ቤት፣የተማሪወች ምኝታ፣የመማሪያ ክፍሎች፣የቤተ ሙከራ መማሪያ ክፍሎች፣የተማሪወች ክሊኒክ እና የማስክ አጠቃቀም ላይ ምልከታቸውን አድርገዋል።
ልዑካን ቡድኑ በምልከታቸው ዩንቨርስቲው በተቀናጀና ሀላፊነት በተሞላበት መልኩ ጥልቃቄ እያደረገ መማር ማስተማሩን እየቀጠለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡