ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በ2015 በጀት ዓመት የተፈቀደለትን የካፒታል እንዲሁም የመደበኛ በጀት ላይ የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ውይይት አደረገ

ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በ2015 በጀት ዓመት የተፈቀደለትን የካፒታል እንዲሁም የመደበኛ በጀት ላይ የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ውይይት አደረገ።
በዉይይቱ ላይ ዳይሬክተሩን ጨምሮ የኮሌጅ፣የመማሪያ ሆስፒታል እንዲሁም የመዓከል የሂሳብ ሰራተኞች   ተገኝተዋል ።
 የዉይይቱም አላማ በ2015 በጀት ዓመት ከኦዲት ግኝት የጠራ እና ግልፀኝነት የተሞላበት አሰራር እንደሚተገበር እንዲሁም ጠንካራ የፋይናንስ ፍሰት እንዴት ማስቻል እንደሚቻል ላይ ያተኮረ ነዉ።
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ቦሩ ሂርባዬ እንዳሉት በበጀት ዓመቱ ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለበጀት ዓመቱ የተያዘ ካፒታል በጀት እና መደበኛ በጀት አሳዉቀዉ ሁሉም ኮሌጆች እንዲሁም ዳይሬክተሮች በሃላፊነት እና ተጠያቂነት በተሞላ መልኩ ያቀዱትን እና ከእቅድ በላይም እንዳይጠቀሙ በተጨማሪም የኮሌጅም ይሁን የእያንዳዱ ዳይሬክቶሬት  የሂሳብ ሰራተኞች ይሄንን ሂደት እንዲከታተሉ አሳስበዋል።
የየኮሌጅ፣የመማሪያ ሆስፒታል እንዲሁም የመዓከል የሂሳብ ሰራተኞችም የ2015ዓ.ም በጀትን ከምንም የኦዲት ግኝት የፀዳ እና የፋይናስ ስረዓቱን የጠበቀ እንዲሆን ዳይሬክተሩ አሳስበዋል ።
ለላቀ ለዉጥ እንተጋለን !
ሕምሌ 04/2014 ዓ.ም
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ