በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና እንዲፈተኑ የተመደቡ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ መዕከሉ እየገቡ ይገኛሉ።

ሀምሌ 06/2016 ዓ/ም

በዩኒቨርሲቲዉ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና እንዲፈተኑ የተመደቡ ተማሪዎች ከዛሬ ሀምሌ 06/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 5;30 ጀምሮ ከዙሪያዉ ከሚገኙ ዞኖችና ወረዳዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ቅጥር ግቢ እየገቡ ሲሆን፣ በሁለተኛ ዙር ለፈተናዉ የሚቀመጡ ተማሪዎች ብዛት ወንድ 4624 ሴት 2200 በጥቅሉ 6824 ናቸዉ።  ለተማሪዎቹ በተደረገዉ የአቀባበል ስረዓት ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንቶችና የስራ አመራሮች ሲሆኑ አቀባበሉን በምርቃት የከፈቱት የአካባቢዉ አባገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ናቸዉ።

በወጣዉ የፈተና መረሀ ግብር መሰረት የሁለተኛዉን ዙር ፈተና የሚወስዱት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሆኑ ዩኒቨርሲቲዉም በበኩሉ አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ለተማሪዎቹ እንኳን በሰላም መጣችሁ በማለት አቀባበል እያደረገ ይገኛል።

በሌላ በኩል ተማሪዎቹ በፈተናዉ መዕከል በሚያደርጉት ቆይታ ዩኒቨርሲቲዉ የምግብ፣ የመኚታና የህክምና እንዲሁም ተጓዳኝ ግብዓቶችን በማሟላት ተፈታኞችን እያስተናገደ ይገኛል።