በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በ"College of Natural and Computational Science" የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ ተከሄደ ነው፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 01/2017(BHU)
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራትንና አግባብነትን ለማስጠበቅና ለማረጋገጥ እየተደረገ ባለው ጥረት ውስጥ የራሱን ድርሻ ለመወጣት የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ከሚሠጣቸው የትምህርት ክፍሎች መካከል በተወሰኑቱ ላይ የሥረዓተ ትምህርት ክለሳ እያደረገ ይገኛል። በያዝነው የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲው ባሉት የተለያዩ ኮሌጆች በሚሰጡ የትምህርት ፕሮግራሞች ዙሪያ የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ እየተደረገ ነው፡፡
በዚሁ መሰረት በ " College of Natural and Computational Science ስር በሚሰጡት የ2ኛ ድግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች ዙሪያ የየትምህርት ክፍሉ መምህራንና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት የሥርዓተ ትምህርት ክለሳዉ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የሥርዓተ ትምህርት ክለሳው ከተደረገባቸዉ የትምህርት መስኮች መካከል "Msc degree in Mining, Geology Msc degree in Health and Physical Fitness, Msc degree in Environmental Science, Msc degree in nuclear physics & Msc degree in Mathematical Modeling and differential Equation" ናቸዉ፡፡
በሥርዓተ ትምህርት ክለሳ ሂደት ላይ ከተሳተፉ የትምህርት ባለሙያዎች መካከል በየዘርፉ ልምድ ያላቸዉ ምሁራንና እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲዉ ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች የተሳተፉ ሲሆን በተጨማሪ ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም የተለያዩ ምሁራን በበየነ መረብ በመሳተፍ በሥረዓተ ትምህርት ክለሳ ላይ ያላቸውን ልምድ አካፍሏል፡፡