በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዙር የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና አስጣጥና ስነ-ስረዓትን በተመለከተ ኦረንቴሽን ተሰጠ።

ሀምሌ 08/2016 ዓ/ም

በዩኒቨርሲቲዉ በሁለተኛ ዙር ፈተናዉን ለሚወስዱ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የፈተናዉን አሰጣጥና ስነ-ስረዓትን በተመለከተ በዩኒቨርሲቲዉ ቅጥር ግቢ ኦረንቴሽን የተሰጠ ሲሆን፣ ኦረንቴሽኑን የሰጡት የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ ሲሆኑ በተሰጠዉ ኦረንቴሽን ተማሪዎቹ በፈተናዉ ወቅት መከተልና ማክበር የሚገባቸዉን ህጎችና ስነ-ስረዓቶች በተክክል እንዲገነዘቡ ተደርጓል።

በተመሳሳስይ መልኩ ከፈተና አሰጣጥና ሂደት ጋር ተያይዞ በዩኒቨርሲቲዉ ፈተናዉን እንዲሰጡ ተመድበዉ ለተላኩ መምህራን ፈተናዉን በተመለከተ አጠር ያለ ዉይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ምክክር የተካሄደ ሲሆን፣ ቀደም ሲል በማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ወቅት የታየዉን ጠንካራ ጎን እንዲያስቀጥሉና በተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ጊዜም እንዲሁ በበለጠ የፈተና ስነ-ምግባርና ስነ-ስረዓት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በተደረገዉ የመድረክ ምክክር መግባባት ላይ ተደርሷል።