በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛው ዙር የተቆጣጣሪዎችና የመረጃ ሰብሳቢዎች ለግብርና ቆጠራ ለተመደቡ ባለሙያዎች አጠቃላይ ገለጻ ተሰጠ።

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ፣ ነሐሴ 19፣ 2016 ዓ/ም (BHU)

ከሱማሌ ክልል ሊበን፤ምስራቅ ቦረና፤ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች ዉስጥ ከሚገኙ ቀበሌዎች፣ የከተማ መስተዳድርና ወረዳዎች ለሶስተኛ ዙር የተቆጣጣሪዎችና የመረጃ ሰብሳቢዎች ለግብርና ቆጠራ ስልጠና ወደ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ ባለሞያዎች የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ እንዲሁም የማዕከሉ አስተባባሪ አቶ ጌቱ ገ/ስላሴና አሰልጣኖች በተገኙበት በዛሬዉ እለት ስልጠናዉን በሚመለከት አጠቃላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

በገለጻዉ ላይም የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ በመልዕክታቸዉም ይህን በሀገር አቀፍ ደረጃ ወሳኝ በሆነ መልኩ የሚከናወነዉን ተግባር ለማሳካት ከኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በኩል የተሰጠንን ሃላፊነት በጋራ ለመወጣት ዩኒቨርሲቲዉ የሚሰራ መሆንን በመግለጽ፣ ለሰልጣኖች የሚያስፈልጉ መሰረታዊ የሆኑ አገልግሎቶች መዘጋጀታቸዉም ገልጸዋል።