በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ልዩ የስራ እቅድ ለ60 ቀናት በማዘጋጀት ሲያከናውን የቆየዉን የአፈጻጸም ሪፖርት ገመገመ።

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ታኅሣሥ 3 ቀን 2017 ዓ.ም (BHU)
የአስ/ል/ም/ፕ በዘርፉ ከሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች ስድስት ኮሚቴዎችን በማቋቋም በየዕለቱ የሥራ ክንውን እየገመገመ ክፍተት ባላቸዉ ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ሲያከናውን መቆየቱን ገልጿል፡፡
ሪፖርቱ ሲቀርብ ከነበሩት መካከል የአካ/ምር/ተክ/ሽግ/ እና ማህ/አገ/ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ገበዬሁ አሻግሬ እና የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጌሳ ሞኮና እንዲሁም የተማሪዎች ተወካዮች ፣የዘርፉ ስራ አስፈጻሚዎች፣ ቡድን መሪዎች እንዲሁም የኮሌጅ ዲኖች ናቸው። የሪፖርቱ ይዘትም በተማሪዎች ዶርም የተከናወኑ ተግባራት፣በምግብ ቤት፣በኪሊንክ፣በመዝናኛ፣በፋይናንስ አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ ፣ከምህንድስናና ጥገና አገልግሎት ፣ከንብረት አስተዳደር ፣ከጸጥታና ደህንነት፣ከብቃትና የሰው ሀብት አመራር፣ከግዥ አስተዳደር አንፃር ሲሆን በነዚህ የሥራ ፍሎች በኩል የተሰሩ ዋናዋና ስራዎች ቀርበዋል።
በአፈጻጻም ሪፖርት አቀራረብ ሂደት ላይ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጌሳ ሞኮና በተገኙበት ከተማሪ ተወካዮች ፣ ከሰራተኞች እንዲሁም ከመላዉ ተሳታፊ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ በመስጠት፣ ለተሰሩ ስራዎችም ኮሚቴዎችን በማመስገን ለቀሩት ስራዎች በዚሁ መልኩ በጋራ በመቀናጀት ማስቀጠል አለብን በማለት አስገንዝበዋል።