በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የግብርና እና እንስሳት ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ MSC (open Thesis Defense) እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
Posted by admin on Tuesday, 17 December 2024
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 26/2017(BHU)
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የግብርና እና እንስሳት ሳይንስ ኮሌጅ የሁለተኛ ድግሪ ተመራቂ ተማሪዎች MSc in Agricultural economics, Msc in Soil Science, MSc in Sustainable Natural Resources Management ዙሪያ የመመረቂያ ጽሑፋቸዉን በዛሬዉ ዕለት ማቅረብ ጀምሯል፡፡
በመርሃ-ግብሩ ላይ የግብርና እና እንስሳት ሕክምና ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ዮሐንስ ኡርገሳ ፤ገምጋሚ መምህራንና ሌሎች ተጋባዥ መምህራን የተገኙ ሲሆን ዶ/ር ዮሐንስም በግብርናዉ ዘርፍ የተሻሻሉና በምርምር የተደገፉ የሥራዎችን በመሥራት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
መርሃ-ግብሩ እስከ ህዳር 27/2017 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን አስራ አራት ተማሪዎች ጥናታዊ ጽሑፋቸዉን ያቀርባሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡