በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ “Invigorated Research Agenda and an overview of Research journey`` በሚል ርዕስ ለመምህራን የግንዛበ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
Posted by admin on Tuesday, 17 December 2024
![](https://bhu.edu.et/sites/default/files/styles/large/public/field/image/docg.jpg?itok=c-T65JEZ)
በቡሌ-ሆራ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 26/2017 ዓ.ም (BHU)
በዩኒቨርሲቲዉ ምርምር፤ስርፀትና ሥነ ምግባር ዳይሬክቶሬት አማካኝነት በምርምር ሥራዎች ላይ ያተኮሩ አቅም ግንባታ ሥልጠናዎች እተሰጡ ይገኛሉ፡፡
በዛሬዉ ዕለት በተሰጠዉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ላይ ተገኝተዉ መልዕክት ያስተላለፉት የአ/ምር/ማህ/አገ/ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገበየሁ አሻግሬ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ደረጃ የሚሠሩ የምርምር ሥራዎች በሦስት ዋና ዋና ነጥቦች ማለትም በመማር ማስተማር፤በምርምር እና በማህብረሰብ አገልግሎት ላይ የሚያተኩሩ መሆናቸዉን ገልፀዋል፡፡
አያይዘዉም ዶ/ር ገበየሁ ምርምርን አስመልክቶ እስከ አሁን ሲሰሩ የነበሩት የምርምር ሥራዎች በተበጣጠሰ መልኩ በመሆን በተፈለገዉ ልክ ዉጤት ያላስገኙ መሆናቸዉን በመግለጽ ይህን በማስቀረት በአንድነት መሥራቱ ጊዜና ገንዘብን ከመቆጠቡም ባሻገር የተሻለ የምርምር ሥራ ለመሥራት የሚያስችል መሆኑን ጠቅሷል፡፡
የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዉን የሰጡት ምርምር፤ስርፀትና ሥነ ምግባር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር አብነት በቀለ ሲሆኑ ሌሎች መምህራንም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሉትን ተሞክሮዎች በማቅረብ የጋራ ዉይይት ተደርጓል፡፡