በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ YOLK ከተባለው ግብረሰነይ ድርጅት ጋር በመተባበር በምዕራብ ጉጂ ዞን ሀምበላ ዋመና ወረዳ በጮርሶ ሶዱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፀሐይ ሃይል የሚሠራ የሶላር ኃይል ማመንጫ አገልግሎት አስጀመረ።
Posted by admin on Friday, 17 January 2025

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም (BHU)
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህብረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት YOLK ከተባለ ከደቡብ ኮሪያ ድርጅት ጋር በመተባበር በምዕራብ ጉጂ ዞን በሀምበላ ዋመና ወረዳ የኤሌክትርክ ኃይል ካልተዳረሰባቸው ት/ቤቶች አንዱ በሆነዉ ጮርሶ ሶዱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፀሐይ ኃይል የሚሠራ ሶላር ዲሽ በመግጠም ትምህርት ቤቱንና ማህብረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት የግብረሰናይ ሥራን ለመሥራት ‹‹SOLAR COW››የሚል መጠሪያ ካለው ሌላ ድርጅት ጋር አብሮ ለመስራት ተፈራርሞ ወደ ስራ እንደገባ ታውቋል።
የሶላር ኃይል ማመንጫው ሊገሳ ዋናው ዓላማ የተማሪዎችን መጠነ ብክነት ለመቀነስ፣የአከባቢው ማህበረሰቡና ቤተሰቦቻቸው በማታ የመብራት ሃይል እንዲያገኙ ለማድረግ ሆኖ በሌላ በኩል የትምህርት ጥራትንም ለመደገፍና ማሻሻል ላይ ያተኮረ ነዉ።
የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህብረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተሩ እንደገለጹት የጮርሶ ሶዱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር፣መምህራን፣ተማሪዎች እንዲሁም የአካባቢዉ ማህበረሰብ በተገኙበት የሶላር ስረዓቱን አስጀምረናል ብለዋል።
ፕሮግራሙ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት መ/ር ንጉሴ ከዚህ በፍትም ዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን እያስተላለፈ የሚገኝ ሲሆን በዛሬዉ እለትም በዚህ ትምህርት ቤት እንዲሁም በቀጣይ ሶስት ት/ቤት YOLK ከተባለው ድርጅት ባምናገኘዉ የሶላር ዲሽ ተማሪዎቹ ያለምንም የብረሃን ችግር ትምህርታቸዉን እንዲከታተሉ የሚስችል የሶላር ስረዓት /solar system/ለማስተከል አቅደናል ብለዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መ/ር የሆኑት መ/ር ደስታ ገቦ እንደተናገሩት በአካባቢዉ የመብራት ሃይል ባለመኖሩ ተማሪዎቻችን ሳያነቡ እንዲሁም መምህራን የሚሰጧቸውን የቤት ስራ ሳይሰሩ እንደሚመጡ ብሎም መምህራኖቻችን ለሞባይላቸዉ እንኳን ቻርጅ ፍለጋ እስከ አስር ኪሎሜትር እንደሚሄዱ ጠቅሰዉ አሁን ግን ይሄንን ችግር ሁሉ እንደሚቀርፍላቸዉ ተናግረዋል።
ተማሪዎቹም በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተደረገላቸዉ ድጋፍ መደሰታቸዉና ከእንግዲህ ወዲያ ትምህርታቸዉንም በአግባቡ እንደሚከታተሉ ተናግረዋል።















































