በቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ የማተማሪያ ሆስፒታል ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና አገልግሎት ተጠናቀቀ ።
ሀምሌ 17/2016 ዓ/ም
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ የማስተማሪያ ሆስፒታል ከሂማሊያን ካታራክት ፕሮጀክት (HCP) ጋር በመሆን ለአምስት ተከታታይ ቀናት የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና ሲሰጥ ቆይቷል።በስራው ሂደት ካጋጠሙ የተለያዩ ክስተቶች መካከል አንዱ ከአንድ ቤተሰብ አምስት የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህሙማን የተገኙ ሲሆን፣ ለሁለቱ የህክምና እርዳታ ተደርጎላቸዉ ማዬት የቻሉ ሲሆን ሶስቱ ህሙማን ግን ለተጨማሪ የህክምና እርዳታ ወደ ምኒልክ ሆስፒታል የተላኩ መሆናቸው ተገልጿል። በተመሳሳይ መልኩ ሁለቱም ዓይኖቻቸዉ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ያለባቸው 115(አንድ መቶ አስራ አምስት) ህሙማን የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና የተደረገላቸዉ ሲሆን፣በዚህ ዙር በአጠቃላይ በአምስቱ ቀናት ዉስጥ 621 (ስድስት መቶ ሃያ አንድ) ህሙማን የህክምና አገልግሎት ማግኘታቸዉ ተገልጿል።
ይህንን የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ከሶስት የትምህርት ተቋማት የተወጣጡ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ሆኖ፣ አንድ ከአርባምንጭ አንድ ከዋቸሞ እና አንድ ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ የማስተማሪያ ሆስፒታል የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና እስፔሻሊስት ሐኪሞች መሆናቸዉ ታዉቋል።
በመጨረሻም ባለሙያዎቹ ላደረጉት አስተዋጽኦ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሆስፒታሉ የቦርድ አባላት፣ ከ(HCP) የመጡ ሐላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ባሉበት የምስጋና ፕሮግራም ተደርጎ የዚህ ዙር ስራ በዚህ መልኩ መጠናቀቁን የማስተማሪያ ሆስታሉ ቺፍ ኤክስክዩቲቭ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ሳፋይ ኤለማ አስታውቀዋል።