በ2017 የትምህርት ዘመን ለአቅም መሻሻያ (Remedial) ትምህርት ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ታኅሣሥ 7 ቀን 2017 ዓ.ም (BHU)
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በ2017 የትምህርት ዘመን ለአቅም መሻሻያ (Remedial) ትምህርት የተመደቡ ተማሪዎችን ታህሳስ 7 እና 8 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ምዝገባ ለማከናወን በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡
ተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲዉ በሚመጡበት ወቅት ወደ ሁለተኛ ቤታቸዉ የመጡ ዓይነት ስሜት እንዲሰማቸዉ በዩኒቨርሲቲዉ ደረጃ ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች የተወጣጡና የተዋቀሩ ኮሚቴዎች አቀባበል እያደረጉላቸው ይገኛሉ፡፡
የአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱም ተማሪዎቹ ወደ ከተማ ከገቡ በኃላ ከከተማዉ መናኸሪያ ወደ በዩኒቨርሲቲዉ ግቢ የዩኒቨርሲቲው አውቶቡሶች ተማሪዎቹን ከማመላለስ ጀምሮ ከደህንነታቸዉ ጋር ተያይዞ የተከለከሉ ነገሮችን ይዞ እንዳይገቡ ጭምር የተጠናከረ ፊተሻ ማድረግን ያካተተ ስለመሆኑ ተገልጾዋል፡፡
ተማሪዎቹ ከምንም ዓይነት ተጽዕኖዎች ተላቀዉ የመጡበትን ዓላማ ማሳካት እንዲችሉ ከተማሪዎች መሠረታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ አሁን ያለበት ደረጃ ተገምግሞ በሁሉም ረገድ የተሟላ ዝግጅት የተደረገ ሲሆን በዚህ ዙር ይመዘገባሉ ተብሎ የሚጠበቁ ተማሪዎች በማህበራዊ ሳይንስ 913 በተፈጥሮ ሳይንስ 1282 መሆናቸዉን ከአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡