ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲቲና የኢትዮጵያ ደን እና ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 07/2018 ዓ.ም ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ
ዩኒቨርሲቲው በአካባቢው ያለውን ብዝሃ ሕይወት በአግባቡ በመጠበቅ ከቱርዝም የሚገኘው ገቢ የሀገር ኢኮኖሚን መደገፍ እንዲችል ከደን እና ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ከባልሥጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኩመራ ዋቅጀራ ጋር የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ፣ምርምር፣ቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህብረሰብ አግልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገበየሁ አሻግሬ ተፈራርሟል።
ም/ፕሬዝዳንቱ ስምምነት መርሃ ግብሩ በተካሄደበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በጋራ ለመስራት ስምምነት መፈፀሙ የመጀመሪያ ምዕራፍ መሆኑን፣ነገር ግን ሥራው ገና በመሆኑ ያለንን አቅሞች በጋራ በመጠቀም የሚታይ ሥራ መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ የገለፁ ሲሆን ከታቋማት ጋር በትብብር መሥራት የሚለው ዩኒቨርሲቲው በቁልፍ ተግባራት ደረጃ ለማከናወን ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ከተስማማቸው ሥራዎች መካከል አንዱ ስለመሆኑም አንስቷል።
ዋና ዳይሬክተሩ በበኩላቸው አካባቢው ሰፊና እምቅ የተፈጥሮ ፀጋ ያለበት አካባቢ በመሆኑ ይህንኑ በአግባቡ ለመጠበቅ በምርምር ሰፊ አቅምና ልምድ ካለው ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጋር መስራቱ ውጤታማ የሚያደርግና ከአርብቶ አደር አካባቢ ማህብረሰብ የአኗኗር ሁኔታ እየተቀየረ ከመምጣቱ ተያይዞ በቦረና ብሄራዊ ፓርክ ቁጥራቸው እየተመናመነ የመጣውን አዕዋፋት ዝሪያዎችን ለመታደግ ጭምር የጋራ ሥራ ስምምነቱ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል።
ሥራው በበላይነት የሚፈፀመው በግብርና ኮሌጅ ሲሆን የኮሌጁ ዲን ዶ/ር አንጋሳ እና የብዝሃ ህይወት እና ኢኮቱሪዝም ት/ክፍል ሃላፊ
መ/ር በላይ ማሩ በቀጣይ በሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቷል።














































