ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለመምህራንና ለትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናን በሚመለከት የግንዛቤ ማስጨበጫ ኦረንቴሽን ሰጠ።
ሀምሌ 22/2016 ዓ/ም
ወደ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለሙያ ማሻሻያ ትምህርትና ስልጠና የተላኩትን የትምህርት ቤት ዳይሬክተሮች እንዲሁም የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራንን ስልጠና አስመልክተዉ ከማዕከል ከክቡር የትምህርት ሚኒስቴር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና ከኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አቢይ አህመድ ለስልጣኞቹ ሰፋ ያለ ማብራሪያና ኦረንቴሽን ከተሰጠ በኋላ ዩኒቨርሲቲዉም በበኩሉ ለስልጣኞቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፈ ሲሆን፣ ሰልጣኞቹም በዩኒቨርሲቲዉ በሚኖራቸዉ የቆይታ ጊዜና የስልጠናዉን ጠቅላላ ሂደት አስመልክቶ በዩኒቨርሲቲዉ ክፍተኛ አመራሮች ተገቢዉ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።በቆይታቸዉም ወቅት ሰልጣኞች የመጡለትን አላማ ለማሳካት ሁሉም ሰልጣኝ በበኩሉ ተገቢዉን ጥረት እንዲያደርግ አስገንዝበዋል።
በተጨማሪም የስልጠናዉን አጠቃላይ ሂደትና የትምህርቱን ይዘት በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያና ገለጻ የተደረገላቸዉ በዶ/ር ለማ ወ/ሚካኤል ሲሆን በግቢዉ ቆይታቸዉም ሁሉም ሰልጣኝ የሚሰጠዉን ትምህርትና ስልጠና በወጉ ተከታትለዉ በመጨረሻም የሚሰጠዉን ምዘናና ግምገማ ማለፍ ብሎም የሚጠበቀዉን የማለፊያ ዉጤት ማስመዝገብ እንደሚጠበቅባቸዉ በማስመር ግልጸዉላቸዋል።
በአጠቃላይ ለዩኒቨርሲቲዉ በተመደበለት የሰልጣኝ ብዛት መሰረት በአሁኑ ሰዓት ዩኒቨርሲቲዉ ተቀብሎ እያስተናገደ ያለዉ ስልጣኝ ብዛት 1385 (አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሰማኒያ አምስት) መሆኑን ከተቀበልነዉ መረጃ መረዳት ተችሏል ።




















































