የቡሌ ሆራ የኒቨርሲቲና የኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 04/2018 ዓ.ም ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ

በቡሌ ሆራ የኒቨርሲቲ አካዳሚክ፤ምርምር፤ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህብረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገበየሁ አሻግሬ የተመራ ልዑክ በዛሬዉ ዕለት አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወት ኢንሲቲትዩት ቢሮ በመገኘት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የግብርና ኮሌጅ ዲን ዶ/ር አንጋሳ ተስፋዬ እና የብዝሃ ህወት እና የኢኮቱሪዝም አያያዝ ትምህርት ክፍል ሃላፊና የዚህ ጉዳይ አስተባባሪ መ/ር በላይ ማሩን ጨምሮ ሌሎችም የተገኙ ሲሆን፣ አካዳሚክ፤ምርምር፤ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህብረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገበየሁ አሻግሬ በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር ዩኒቨርሲቲዉ የልህቀት መስክ አድርጎ እየሠራባቸዉ ካሉት አንዱ በግብርናና በሀገር በቀል ዕዉቀት ላይ በመሆኑ ይህንኑ ሥራችንን በሚደግፍ መልኩ በጋራ ለመሥራት ኢንስቲትዩቱ ፈቃደኛ በመሆኑ ምስጋናቸዉን በማቅረብ በቀጣይ ስምምነቱን በምርምር ጭምር በማሰደገፍ ወደ መሬት ለማዉረድ ዩኒቨርሲቲዉ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል በማለት ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ የብዝሃ ሕይወት ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ደ/ር ካርታ ካስኬ በበኩላቸዉ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከብዝሃ ሕይወት ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ ለመሥራት በመነሳሳቱና በርካታ ኪሎ ሜትሮችን በማቋረጥ ይህን ስምምነት ለመፈፀመ አዲስ አበባ በመገኘታቸዉ ምስጋናቸዉን በማቅረብ ኢንስቲትዩቱ የኢትዮጵያን ብዝሃ ሕይወት በመጠበቅ በዘለቄታዉ ከዘርፉ የሚገኘዉን ጥቅም እዉን ለማድረግ ራዕይ ሰንቆ እየሠራ መሆኑን አስረድቷል፡፡

አያይዘዉም ዳይሬክተር ጄኔራሉ ይህንኑ የጀመረዉን ተግባር ብቻዉን እዉን ማድረግ የማይችል በመሆኑ ከተለያዩ ተባባሪ አካላት ጋር በጥምረት እየሠራ መሆኑንና ከነዚህም አንዱ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በአካባበዉ ያለዉን የብዝሃ ሕይወት ሀብት ለመጠበቅ በዘለቄታዊ መንገድ ለመጠቀም ካሳዩት ተቋማትም የመጀመሪያ መሆኑን በመገለጽ የተደረገዉን ስምምነትም ወደ ተግባር ለመቀየር የቴክኒክ ኮሚቴ አቋቁሞ ወደ ተግባር መግባቱ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በቅርቡም የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ስያሜ ማስተካከያን በሚመለከት በዩኒቨርሲቲዎች ዉስጥ እየተደረገ ባለዉ የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ ጋር ተያይዞ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲም ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት በዩኒቨርሲቲዉ ግብርና ኮሌጅ አስተባባርነት (Biodiversity and Ecotourism Management ) የትምህርት ፕሮግራምን በሚመለከት ከኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወት ኢንስቲትዩት የሥራ ኃላፊወች እና ከአሰር በላይ ዩኒቨረሲቲዎች የተወጣጡ ምሁራን በተገኙበት ወይይት በማድረግ የጋራ ስያሜ ላይ በመድረስ ለትምህርት ሚኒስቴር ግብዓት ስለ መቅረቡ መዘገባችን ይታወሳል፡፡