የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ማጠቃለያ ፈተና (Entrance Exam)የሚወስዱ ተማሪዎችን መቀበል ጀመረ
Posted by admin on Tuesday, 30 July 2024

ዩኒቨርሲቲዉ በ2016 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ማጠቃለያ ፈተና(Entrance Exam)የሚወስዱትን ተማሪዎች በዙሪያዉ ካሉት የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች ተቀብሎ ለፈተናዉ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ እያስተናገደ ይገኛል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በወጣዉ መረሃ ግብር መሰረት ፈተናዉ የሚሰጠዉ በሁለቱም የትምህርት ዘርፍ ማለትም በተፈጥሮ ሳይንስና በማህበረዊ ሳይንስ ሲሆን፣ በቅድሚያ ለማህበራዊ ሳይንስ ተከታታይ ተማሪዎች የሚሰጥ ሆኖ በሁለተኛዉ ዙር ደግሞ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ለፈተናዉ እንደሚቀመጡ ዩኒቨርሲቲዉ ከፌድራል ትምህርት ሚኒስቴር ካገኘዉ መርጃ መረዳት ተችሏል። በዚሁ መሰረት በመጀመሪዉ ዙር ለፈተናዉ የሚቀመጡ የማህበረዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብዛት ወንድ 5736፣ሴት 3828 ድምር 9567 ናቸዉ ።
በተመሳሳይ መልኩ በመቀጠልም የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተናዉን የሚወስዱ ሲሆኑ ብዛታቸው ወንድ 4624 ሴት 2200 ድምር 6824 እንደሆኑ ከዚሁ ከወጣዉ የፈተና ፕሮግራም መረዳት ተችሏል።