ጤና ኢንስቲትዩት ዕጩ ዶ/ር ዳዊት ገልገሎ እና ዕጩ ዶ/ር ሽፈራው ገልቹ የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት (phd) የመመረቂያ የምርምር ጽሑፋቸውን አቀረቡ።

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፣ ግንቦት 22፣2017 ዓ.ም (ቡሆዩ)
ዕጩ የሦስተኛ ዲግሪ(Phd) ተመራቂዎቹ የምርምር ሥራቸውን አዲቫይዜሮቻቸውን ጨምሮ የውጪ ገምጋሚዎችና ሌሎች ተጋባዥ ምሁራን በተገኙበት በማቅረብ በተሳካ ሁኔታ ጨርሰዋል።
በዕለቱም ዩኒቨርሲቲው በም/ፕሬዝዳንት ማዕረግ የጤና ኢንስቲትዩት ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ሳፋይ ኤለማ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን ዕጩ የሶስተኛ ዲግሪ ተመራቂዎች ኢንስቲትዩቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያስመርቃቸው በመሆኑ ለኢንስቲትዩቱም ልዩ ቀን መሆኑን የገለፁ ሲሆን ተመራቂዎቹም በወጣትነት ዕድሜያቸውና በአጭር ጊዜ ለዚህ ስኬት የበቁበት መንገድ ለሌሎች አስተማሪና የይቻላል መንፈስን ያስተማረ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል።
በምርምር ጽሑፍ ግምገማው ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተገኙት ምሑራንም ዩኒቨርሲቲው ለመጀመሪያ ጊዜ በሦስተኛ ዲግሪ የሚያስመርቃቸውን ተማሪዎች ለመገምገም በዩኒቨርሲቲው መገኘታቸው ያስደስታቸው መሆኑን በመግለፅ በቀጣይም ጤና ኢንስቲትዩቱ በሚጠናከርበት ሁኔታ ዙሪያ ወክለው የመጡበትን ዩኒቨርሲቲዎች ተሞክሮ ጭምር ያካፈሉ ሲሆን በቀጣይ ሴት ተመራማሪዎችም እንዲበረታቱ በማለት አስተያየታቸውን ሰጥቷል።
በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምርምር ቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህብረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገበዩሁ አሻግሬ በመዝጊያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ በመገኘት በርካታ ኪ.ሜትሮችን በማቆራረጥ በዩኒቨርሲቲው ለተገኙት ምሑራን ምስጋናቸውን በማቅረብ ጤና ኢንስቲትዩቱ እና ዕጩ ተመራቂዎቹ ባደረጉት ጥረት በተያዘው ትክክለኛ ጊዜ ሠለዳ መሠረት ተመራቂዎቹን ማብቃት መቻሉ አስደሳች መሆኑንም ገልፀዋል።
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲም ለዶ/ር ዳዊት ገልገሎ እና ዶ/ር ሽፈራው ገልቹ የእንኳን ደስ አላችዉ መልዕክት ያስተላልፋል።