Basic Training on Technology Transfer through Power World Simulator and ETAP soft wares for enhancing the Capacity of Lab assistant and Post Graduate Students``በሚል ርዕስ ሥልጠና ተሰጠ

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም (BHU)
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ‹‹Basic Training on Technology Transfer through Power World Simulator and ETAP soft wares for enhancing the Capacity of Lab assistant and Post Graduate Students``በሚል ርዕስ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
ሥልጠናዉ የተዘጋጀዉ በኢንጅነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ስር ከሚገኙት የትምህርት ክፍሎች አንዱ በሆነው በኤሌክትሪካልና ኮምፒዩተር ኢንጅነሪንግ የትምህርት ክፍል አስተባባሪነት ሲሆን በትምህርት ክፍሉ ሥር ያሉትን መምህራን አቅማቸውን በተለያዩ ዘርፎች ለማሳደግና ለማብቃት ታስቦ የተዘጋጀ ሥልጠና መሆኑ በስልጠናው ወቅት ተገልጿል፡፡
በሥልጠናው ሂደትና መክፈቻው ወቅት በቦታው በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉትና በይፋ የከፈቱት የዩኒቨርሲቲዉ የምርምር ስርፀትና ሥነ-ምግባር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር አብነት በቀለ ሲሆኑ በንገግራቸው ወስጥ ከጠቀሷቸው አንኳር ነጥቦች አንዱና ዋንኛው ጉዳይ በአሁኑ ሰዓት በአለም ላይ ያሉ የተለያዩ ድርጅቶች ሥራቸዉን ለማቀላጠፍ፤ዉጤታማ ለመሆንና በትክክለኛ ቁመና ላይ በመሆን ዉሳኔዎች ለመስጠት እንዲያስችላቸዉ የተለያዩ አጋዥ ሶፍትዌሮችን ተጠቅመዉ እየሠሩ መሆናቸዉን ለሥልጠናው ተሳታፊዎች አስገንዝቧል፡፡
አያይዘዉም ዶ/ር አብነት የተለያዩ ተክኖሎጂዎችን በመጠቀም ሥራቸዉን ማከናወን ከሚጠበቅባቸዉ ተቋማት መካከል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዋንኞቹ መሆናቸዉን በመጥቀስ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲም ይህንኑን በመገንዘብ የመምህራንን አቅም በተለያዩ መንገዶች በማሳደግና በማጎልባት የሚገኘዉን አቅም ደግሞ ለመማር ማስተማሩ ሂደት በመጠቀም የተቀላጠፈ ለማድረግና በተለይም ከዩኒቨርሲቲዉ ኢንጅነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ የሚመረቁ ተማሪዎች ዘመኑ ያፈራቸዉን ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም ረገድ ብቁ ሆኖ እንዲመረቁ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብለዋል ። የኮሌጁ ዲን መ/ር ቦሩ ቤደያም በስልጠናዉ አስፈላጊነት ዙሪያ ሰፋ ያለ ሀሳብና መልዕክት ለሥልጠናው ተሳታፊዎች አስተላልፏል፡፡
ሥልጠናዉ በኢንጅነሪንጉ የሥራ ዘርፍ በከፍተኛ ሁኔታ ጥቅም ላይ እየዋሉ ባሉ ወደ አስር በሚጠጉ ሶፍትወሮች አጠቃቀም ዙሪያ በጽንሰ ሀሳብና በእያንዳንዱ ሶፍት ወር አጠቃቀም ዙሪያም በተግባር የተደገፈ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ ሥልጠናው በሁለት ክፊል ተከፍሎ የተዘጋጀ ሲሆን በመጀመሪያ የቀረበው የትምህርቱ ንድፈ ሀሳበዊ ወይም theoretical part ሆኖ በዚሁ ዕለት ደግሞ የትምህርቱን ተግባር ቶኮር ክፍል በላቦራቶሪ በተደገፈ ተምህርታዊ ገለጻ በማድረግ ሥልጠናውን ሰጥቷል