Grant Writing and Project Fund Management በሚል ርዕስ የአቅም ግንባታ ስልጠና Practical Oriented Capacity Building Training/ ለመምህራን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 6/2017 ዓ.ም
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ከተጋበዙ ሙሁራን ጋር ማለትም ከፕሮፈሰር ፍቃዱ ፉፋ እና ዶ/ር ኢንጅ ዋቅጅራ ታካላ ጋር በመሆን በ"Grant Writing and Project Fund Management "በሚል ርዕስ ከህዳር 03/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት /3/ ተከታታይ ቀናት ተግባር ተኮር የአቅም ግንባታ ስልጠና / practical oriented capacity building training/ ለመምህራን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የምርምር፣ ሕትመት፣ስነ ምግባርና ሥርፀት ዳ/ዳይሬክቴር የሆኑት ዶ/ር አብነት በቀለ በንግግራቸዉ ሲያመላክቱ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ የግምጃ ቤት በጀትን በመጠቀም ከ400 በላይ የሚሆኑ የተለያዩ ችግር ፈቺ የምርምር ፕሮጀክቶችን ለአካዳሚክ መምህራን ፈንድ በማድረግ ያሠራ ሲሆን፤ ካለው ዘርፈ ብዙ ችግሮች አንጻር ለምርምር የሚመደበዉ በጀት በቂ እንዳልሆነና ሌላ አማራጭ የገንዘብ ምንጭ ለማፈላለግና ለማግኘት ይህ ስልጠና አስፈላጊ መሆኑን በስልጠናው ላይ ተሳታፊ ለነበሩ የትምህርት ባለሙያዎች /መምህራን/አስገንዝቧል።