Management of Solid and liquid waste ,Health Effect and Personal Safty በሚል ርዕስ ሥልጠና ተሰጠ።
Posted by admin on Saturday, 15 February 2025

የካቲት 05/2017 ዓ.ም
የሥልጠናዉ የበላይ አስተባባር እና የኢንጅነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ዲን መ/ር ቦሩ በዴያ የተዘጋጀዉ ሥልጠና በጋራ በተቀናጀ መልኩ የአካባቢችንን ንጽህና መጠበቅ እንዲንችል አጋዥ የሆነ ሥልጠና መሆኑን አስረድቷል።
አያይዘዉም የኮሌጁ ዲን የሥልጠናውን ዋና ዓላማ ሲገልጹ በተቋማችን የሚታየዉን የደረቅና የፈሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ችግሮችና ክፍተቶችን በተቀናጀ መልኩ ማስወገድና የዘመነ እንዲሆን በማድረግ የመማር ማስተማር ሥራን መደገፍ እንደሆነም ተናግሯል።
በሥልጠና ቦታ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲዉ አካዳሚክ ፤ምርምር፤ቴክኖሎጅ ሽግግር እና ማህብረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገበየሁ አሻግሬ የተለያዩ ሙያ ባለቤት የሆኑ አካላት ሰብሰብ ብሎ በጋራ ለአንድ ዓላማ መሥራት ዉጤታማ የሚያደርግ መሆኑን በመግለጽ በተበታተነ መልኩ የሚወጣዉን ወጪ እንደሚቀንስም ተናግሯል።
የዩኒቨርሲቲዉ አስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጌሳ መኮና በበኩላቸው የተቋሙን የውስጥ ችግር በራስ አቅም ለመፍታት ታስቦ የሚከናወኑ ተግባራት መኖራቸዉ የሚደነቅ መሆኑን አስረድቷል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተቋማችን ውስጥ ባሉት ልምድ ባላቸዉ መምህራን እየተሰጡ ያሉ ሥልጠናዎች ብዙ ወጪ የሚያስቀር መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ነጌሳ በአሁኑ ሰዓትም የኢንጅነሪንግና ቴክኖሎጅ ኮሌጅ ከጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ተቋሙ ለመማር ማስተማሩ ሂደት ምቹና ጽዱ እንዲሆን ታሳቢ በማድረግ ያዘጋጁት ሥልጠና የጋራ ተቋምን ችግር በጋራ የመፍታት ዓላማን የተከተለ ስለመሆኑ ተናግሯል።
አያይዘዉም ዶ/ር ነጌሳ የተጀመሩ ተመሳሳይ ሥራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸዉን በመግለጽ በቀጣይ ለተቋሙ ገቢ በሚያመነጩ እና የማህብረሰቡን ችግር በሚፈቱ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ይደረጋል ብሏል።
በሥልጠናዉ ሂደት ከሁለቱም ሥራ ክፍሎች መካከለኛ አመራሮችን ጨምሮ የኬሚካል ኢንጅነሪንግ፤ኢንቫይሮሜንታል ኢንጅነሪንግና የዉሃ ሀብት ልማት ኢንጅነሪንግ መምህራን ተሳታፊ ስለመሆናቸው ተጠቅሷል።