የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በቡሌ ሆራ ከተማ ለሚገኙ የጽዳት እና የምግብ ዝግጅት ባለሙያዎች በተላላፊ በሽታዎች መከላከል ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በቡሌ ሆራ ከተማ ለሚገኙ የጽዳት እና የምግብ ዝግጅት ባለሙያዎች በተላላፊ በሽታዎች መከላከል ዙሪያ ስልጠና ሰጠ
የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲው የጤና ኢኒስቲትዩት ጋጋር በመተባበር ባዘዘጋጀው ስልጠና ላይ ከ60 በላይ የሚሆኑ ሰልጣኞች ተሳትፈዋል።
ሰልጣኞቹ በጤና ተቋማት የሚሰሩ የጽዳት እና የምግብ ዝግጅት ባለሙያዎች ሲሆኑ፤ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል በሚያስችሉ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ በጤና ባለሙያዎች ስልጠናው ተሰጥቷቸል።
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የጤና ኢኒስቲትዩት፣ የምርምርና ማሕበረሰብ አገልግሎት እና ቴክኖሎጅ ሽግግር ዳይሬክተር መ/ር ፍጹም ደምሴ እንደገለፁት 'ስልጠናው የጽዳትና የምግብ ዝግጅት ባለሙያዎችን እንዲሁም ተገልጋዮችን ለተላላፊ በሽታዎች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ለማድረግ የታሰበ ነዉ'።
ስልጠናው የተካሄደው በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ማስተማሪያ ሆስፒታል በሚገኘው አዳራሽ ሲሆን፤ በተለያዩ ለማህበረሰብ ጠቀሜታ ባላቸው ጽንሰ ሀሳቦች ላይ በርካታ ስልጠናዎች በዩኒቨርሲቲው የማሕበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ሲሰጡ መቆየታቸው ይታወሳል።
በተያያዘ ዜና ዩኒቨርስቲው በቡሌ ሆራ ከተማ ለሚገኙ ለግል የጤና ተቋማት ባለቤቶች፣ ለግል ፋርማሲ ባለቤቶች፣ እንዲሁም ለግልና ለመንግሥት ጤና ተቋም ሠራተኞች በ'Antibiotics resistance' ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የጤና ኢኒስቲትዩት ዲን መ/ር ታከለ ኡቱራ "ከጥራት በታች የሆኑ እና በኮንትሮባንድ የሚገቡ መድሀኒቶች እንዲሁም ያለ ባለሙያ ትዕዛዝ የሚሸጡና የሚገዙ መድሀኒቶች ለማሕበረሰብ ጤና ጠንቅ ስለሆኑ 'Antibiotics Resistance'ን ተግባራዊ ማድረግ የሁላችንም ግዴታ ነው' ብለዋል።
የ'Antibiotics Resistance' መመሪያዎች ተግባራዊ እንዲሆኑ በሚያስችሉ ሀሳቦችና ትኩረት በሚሹ ጤና ነክ ጉዳዮች ላይም ጥልቅ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
ለላቀ ለዉጥ እንተጋለን !!!
ሕዳር 2014 ዓ.ም
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ