በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ(BHU) ጥቅምት 04/2017 ዓ.ም

ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረዉን ብሄራዊ የሰንደቅዓላማ ቀን ምክንያት በማድረግ በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲዉ ሠራተኞች፤የተለያዩ የፀጥታ አካላት እና ለአቅም ግንባታ ሥልጠና ወደ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሥልጠና ማዕከል የገቡ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ጭምር በተገኙበት ሰንደቅዓላማዉ ብሔራዊ ክብርን በጠበቀ መልኩ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ፤መዝሙር ተጅቦ እንዲሠቀል የተደረገ ሲሆን በሰንደቅዓላማው ቀን ላይ የተሳተፉ አካላት ቃለ መሃላ በመግባት ወይም በመፈጸም ሥነሥረዓቱ ተጠናቋል ፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲትዩት እና ግብርና ኮሌጅ ለተመለመሉ መምህራን ሥልጠና ተሰጠ፡፡

መስከረም 26/2017

`Integration of One health approaches and principles in to Teaching, Research, and Community services`በሚል ርዕስ ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከግብርና ኮሌጅ ለተመለመሉ መምህራን ሥልጠና ተሰጠ፡፡

ሥልጠናዉ የተዘጋጀዉ `COHESA` Capacitating one Health In Eastern and Southern Africa` በሚል ድርጅት ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን በሥልጠናዉ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማን ጨምሮ ሌሎች የዩኒቨርሲቲዉ ከፍተኛ አመራሮችም ተገኝቷል፡፡

ማስታወቂያ

ውድ የተከበራችሁ የዩኒቨርሲቲያችን መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ለ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን በሠላም አደረሳችሁ እያልን የሁለተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ መደበኛ የመጀመሪያ ዲግሪና ነባር የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የቅበላ ቀን በEBC እንዲሁም በዩኒቨርስቲው ማህበራዊ ሚዲያ (Facebook እና Telegram) ጥሪ እስኪተላለፍ ድረሰ በትእግስት እንድትጠብቁ በአክብሮት ለመግለጽ እንወዳለን ።

 

Pages