የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለዩኒቨረሲቲው በተለያየ ክፍል ባለሙያዎች እና የሰዉ ሀብት ልማት አስተዳደር ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።

የስልጠናው ትኩረት ከኦዲት ግኝት የፀዳ ተቋም ለመፍጥር በሚያስችሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲሆን፤ በገንዘብ ሚኒስቴር የኦዲት ኢንስፔክሽን ባለሙያ በአቶ መኮንን መኩሪያ ስልጠናው ተሰቷል።
የበጀት ክትትል፣ የተከፋይ ሂሳብ፣ የግዥ፣ የንብረት አያያዝና አጠባበቅ ስርዓት እንዲሁም ሌሎች ተመሳሳይ የፋይናንስ አጠቃቀም እና አተገባበር የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች በስልጠናው ዉስጥ ተካተዋል።
የገንዘብ ሚኒስቴርን ደንብ እና መመሪያ ህጉን በጠበቀ መልኩ የፋይናንስ ስርዓቱን ለማክበርና ለማስከበር በሚያስችሉ ፅንሰ ሀሳቦች ላይም ሰፊ ማብራሪያ ተሰቶባቸዋል።
በዪኒቨርሲቲው በተከሰቱ የኦዲት ግኝቶች ዙሪያም የዩኒቨርሲቲው የፋይናንስ፣ የግዥ እና የንብረት አስተዳደር ባለሙያዎች ተቋሙ በከፍተኛ የለውጥ ጉዞ ላይ በመሆኑ፤ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት እንዳጋጠመ አስታውሰው የተቋሙን የፋይናንስ ስርዓት ለማዘመንና ከኦዲት ግኝት የፀዳ ተቋም ለመፍጠር ሰፋፊ ሥራዎችን መሥራት መጀመራቸውን ተናግረዋል ።
በስልጠናዉ ላይ በተቋሙ የተገኙ የኦዲት ግኝቶች ለሠልጣኞች የተገለፁ ሲሆን፤ በግኝቶች ላይም ውይይቶች እና ሙያዊ ማብራሪያዎች ተሰጥቶባቸዋል።
የ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት አፈፃፀም ከባለፉት ጊዜያት የተሻለ ለማድረግና የተቋሙን የፋይናንስ አሰራሩን ለማዘመን እየተሰራ ስለመሆኑም ተገልጿል።
ለላቀ ለዉጥ እንተጋለን !!!
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ