ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ፣ ነሐሴ 15፣ 2018 (ቡሆዩ)-በቡሌ በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ትምህርት ቤት የዩኒቭርሲቲውን 2ኛ ደረ ጃ ትምህርት ቤትን ጨምሮ በቡሌ ሆራ ከተማ ለሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ለተመለመሉ ጎበዝ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ይገኛል።
የመርሃ ግብሩ መዘጋጀት ዓላማው በከተማዋ የሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና በዩኒቨርሲቲው ያሉ ልዩ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት ከክፍላቸው ከ1ኛ እስከ 10ኛ ደረጃ የሚወጡ እና ከፍተኛ ውጤት ያላቸውን ተማሪዎች በትምህርታቸው የበለጠ እንዲጠነክሩና በቀጣይ የትምህርት ጉዟቸው ስኬታማ እንዲሆኑ ከአሁኑ ማዘጋጀት አስፈላጊ በመሆኑ የተዘጋጀ መርሃ ግብር መሆኑ ተገልፆዋል።
እየተሰጡ ያሉት የትምህርት ዓይነቶች በዋናነት የተፈጥሮ ሳይንስ ማለትም ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስና ሒሳብ ሲሆን ማህበራዊ ሳይንስና ኢኮኖሚክስን ጨምሮ በዩኒቨርሲቲው መምህራን በበጎ ፈቃድ አገልግሎት መልክ እየተሰጡ መሆናቸው ተገልፆዋል
ስለ ፕሮግራሙ መግለጫ የሰጡት የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ትምህርት ቤት ዲን ዶ/ር ነጋ ባልቻ፣ ይህ አጋዥ የትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎቹ በብሔራዊ ፈተና ስኬታማ እንዲሆኑ ጥሩ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።
ቡሌ ሆራ ዩኒቭርሲቲ
