በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና እንዲፈተኑ የተመደቡ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ መዕከሉ እየገቡ ይገኛሉ።
Posted by admin on Tuesday, 30 July 2024በዩኒቨርሲቲዉ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና እንዲፈተኑ የተመደቡ ተማሪዎች ከዛሬ ሀምሌ 06/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 5;30 ጀምሮ ከዙሪያዉ ከሚገኙ ዞኖችና ወረዳዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ቅጥር ግቢ እየገቡ ሲሆን፣ በሁለተኛ ዙር ለፈተናዉ የሚቀመጡ ተማሪዎች ብዛት ወንድ 4624 ሴት 2200 በጥቅሉ 6824 ናቸዉ። ለተማሪዎቹ በተደረገዉ የአቀባበል ስረዓት ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንቶችና የስራ አመራሮች ሲሆኑ አቀባበሉን በምርቃት የከፈቱት የአካባቢዉ አባገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ናቸዉ።