የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ/ም የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት የሚወስዱ የ”STEM”ተማሪዎችን መቀበል ጀመረ

ሀምሌ 27/2016 ዓ/ም

በዙሪያዉ ካሉት የተለያዩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ እነዚህ ተማሪዎች ከየትምህርት ቤታቸዉ በትምህርት አቀባበላቸዉ ከሌሎች የተሻሉና እንዲሁም የፈጠራ ዝንባሌ ያላቸዉ ወይም ልዩ ፍላጎት /Special Gift /talency/ ያላቸዉ መሆናቸዉን ቀደም ሲል ከነበረዉ የተማሪዎች ፕሮፋይል መረዳት ተችሏል።

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የክረምት በጎ አድራጎት ስራ በዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎች አስጀመረ።

ሀምሌ 27/2016 ዓ/ም

የሰላም ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በ2016 በጀት ዓመት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሰጡ ቀደም ሲል በዩኒቨርሲቲዉ ደረጃ አሰልጥኗቸዉ የነበሩትን ተማሪዎች በማስተባበርና በመምራት የክረምት የበጎ አድራጎት ስራ /አገልግሎት/ እንዲሰጡ ከሀምሌ 27/2016 ጀምሮ የዩኒቨርሲቲዉን አጠቃላይ ቅጥር ግቢና የማስተማሪያ ሆስፒታል በማጸዳት አገልግሎቱን አስጀምረዋል።  የበጎ አድራጎት አገልግሎቱን ለማስኬድ በተቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት የዩኒቨርሲቲዉ ክፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የዘመቻዉ አላማና ግብ በበጎ አድራጎት ስራ ላይ ለተሳተፉ ተማሪዎች ስፋ ያለ ገለጻ የተሰጠ ሲሆን፣የበጎ አድራጎት ስራዉም በቀጣይነት በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች መካከል በማዝመትና በመሰማራት እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል።

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ልማት ማዕከል የስንዴ ምርት መሰብሰብ መጀመሩን ገለፀ፡፡

ሀምሌ 27/2016 ዓ/ም

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ልማት ማዕከል እንደገለጸው በ2016 የምርት ዘመን ሁለት አይነት የስንዴ ምርጥ ዘርና የግብርና ግብዓት በመጠቀም መዝራቱን አስታውሰው የተዘራዉም የስንዴ ዘር ዘመናዊና ምርጥ ዘር መሆኑን ገልጸው አይነታቸውም "ቀቀባ" ና "ኪንግባርድ" የተባሉ መሆናቸውን አስታውሰዋል። የስንዴ ምርቱ የተሰበሰበውም ዘመናዊ የምርት መሰብሰቢያ መሣሪያ በመጠቀም እንደሆነ የማዕከሉ ዳይሬክተር መ/ር ቀመር ይማም ገልፀዋል፡፡ ይህ የማምረቱ ሂደት ወደፍት ተጠናክሮ ከቀጠለ ለዩኒቨርሲቲዉ በገቢ ምንጭነት ከማገልገሉም በላይ ለመማር ማስተማር ፤ለምርምር ; ለቴክኖሎጂ ሽግግርና ለማህብረሰብ አገልግሎት ከፍተኛ ጥቅም ያለዉ መሆኑን በአንክሮ ገልጸዋል፡፡

ማስታወቂያ

ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 የትምህርት ዘመን የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ላላቸው አመልካቾች የሚሰጠው የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና  (NGAT) ምዝገባ የሚካሄደው ከሐምሌ 24 - ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ የመመዝገቢያው ቅጽ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሟሟላት በ https://NGAT.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

 

Pages