በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የፀረ-ጾታ ጥቃት፤የፀረ-ኤድስ እና የአካል ጉዳተኞች ቀን ተከበረ፡፡
Posted by admin on Friday, 17 January 2025ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም (BHU)
በዚህ አመት የፀረ-ፆታ ጥቃት በአለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ ‹‹የሴቷ ጥቅት የእኔም ነዉ ዝም አልልም! ›› በሚል መሪ ቃል፤ በሌላ በኩል የፀረ-ኤድስ ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ37ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ36ኛ ጊዜ ‹‹ሰብዓዊ መብት ያከበረ ኤች አይ ቭ አገልግሎት ለሁሉም!›› እንዱሁም የአካል ጉዳተኞች ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ32ኛ ጊዜ ‹‹የአካል ጉዳተኞችን የመሪነት ሚና በማጉላት አካታችና ዘላቂ ልማትን እናረጋግጥ!››በሚል መሪ ቃል የዩኒቨርሲቲዉ የሥራ ኃላፊዎች ፤ሰራተኞችና ተማሪዎች በተገኙበት በተለያዩ መርሃ ግብሮች ታጅቦ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡