በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የችግኝ ተከላና የምስጋና ፕሮግራም ተካሄደ።
Posted by admin on Tuesday, 30 July 2024በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና የተፈተኑ ተማሪዎች ፈተናዉን እንዳጠናቀቁ ሀገር አቀፍ የአረጉጓዴ አሻራ ፕሮግራምን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ዉስጥ የረሳቸዉን ድርሻ ለመወጣት በዩኒቨርሲቲዉ ግቢ ዉስጥ የተለያዩ ዛፎችን ተከሉ። በሀገር አቀፍ በተቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት የመጀመሪያ ዙር ተፈታኝ የሆኑት የማሃበረዊ ሳይንስ ተማሪዎች በችግኝ ተከላዉ ላይ የተሳተፉ ሲሆን በተመሳሳስይ መልኩ በሚቀጠለዉ ሳምንት ለፈተናዉ የሚቀመጡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችም የአረንጓዴ አሻራዉን የማስቀጠልና የመተግበር ፕሮግራም እንደሚያካሂዱ ከወጣዉ ፕሮግራም ለመረዳት ተችሏል።