ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ

ጥቅምት 07/2016 ዓ.ም
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች የተረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ  አመልካቾችን ባሉት ክፍት ስራ ቦታዎች /ለአካዳሚክ መምህርነት/ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል። ስለሆነም
የሁሉም የስራ መደቦች የቅጥር ሁኔታ በውል ሆኖ በከፍተኛ ትምህርት ተቋም አስራር መሰረት ይሆናል
የደሞዝ ሁኔታ- በክፍተኛ ትምህርት ተቋማት የደሞዝ ስኬል መሰረት
ሴት ተወዳዳሪዎች ይበረታታሉ
ለወንድ MA/MSc (ሁለተኛ ዲግሪ) አመልካቾች CGPA 3.5 እና ከዚያ በላይ ሆኖ የመጀመሪያ ዲግሪ CGPA 3.0 እና ከዚያ በላይ ያለው
ለሴት  MA/MSc (ሁለተኛ ዲግሪ) አመልካቾች የMA/MSc CGPA 3.35 እና ከዚያ በላይ ሆኖ የመጀመሪያ ዲግሪ CGPA 2.75 እና ክዚያ በላይ ያላት
ለወንድ የመጀመሪያ ዲግሪ (BA/BSc) አመልካቾች የመጀመሪያ ዲግሪ CGPA 3.25 እና ከዚያ በላይ ያለው
ለሴት የመጀመሪያ ዲግሪ (BA/BSc) አመልካቾች የመጀመሪያ ዲግሪ CGPA 3.0 እና ከዚያ በላይ ያላት
ሁሉም አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁን ኮፒውን እና CV በመያዝ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን  (ማለትም ከ07/02/2016 ዓ.ም) ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት በአካል በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ በሰው ሃብት ልማት ቢሮ ቁጥር 159 ወይም በፖ.ሳ.ቁ 144፣ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ  በመላክ መመዝገብ ይችላሉ።
የተመረጡ ብቁ ተወዳዳሪዎች ለቃለ መጠይቅ የሚቀርቡ ሲሆን ቀኑንም ለተመረጡ ተወዳዳሪዎች የምናሳውቅ ይሆናል። 
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ