የተማሪዎች የጥሪ ማስታወቂያ ለውጥ

ጥቅምት 28/2016 ዓ.ም
በ2015 ዓ.ም በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች እና በ2014 ዓ.ም ትምህርት ጀምራችሁ በአንደኛ ሴሚስተር በውጤት እና በተለያዩ ምክኒያቶች ዊዝድረዋል (Withdrawal) በመሙላት ላቋረጣችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በ2015 ዓ.ም በተሰጠው የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ት/ት ሚኒስቴር በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የመደባቸው ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ህዳር 1 እና 2/2016 ዓ.ም የተባለው ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑንና በቅርቡ የምናሳውቃችሁ መሆኑን እንገልጻለን።
ቡሌ ሆራ ዩንቨርሲቲ