የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሣይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በሱሮ ወረዳ ለሚገኝ ሜዲባ በርጉዳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ለአቅመ ደካማ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

ሰኔ 02/2015
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሣይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በሱሮ ወረዳ ለሚገኝ ሜዲባ በርጉዳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ለአቅመ ደካማ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉ የተገኘዉ የማህበራዊ ሣይንስና ሥነ-ሰብ ኮሌጅ ዉስጥ መ/ር የሆኑት ዶ/ር Sinarayar Britto  ካናዳ ሀገር ከሚገኝ OFT (Ontario Teachers Federation) ጋር በመነጋገር የተገኘ ሲሆን የኮሌጁ ዲን የሆኑት መ/ር ሾልሳ ጂሎ በት/ቤቱ በመገኘት የትምህርት ቁሳቁስ በማስረከብ ለተማሪዎቹም መልዕክት አስተላልፏል፡፡ 
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ

3rd round international conference was held at Bule Hora University.

May 25/2015
3rd round international conference was held at Bule Hora University.
The 3rd round of international conferences was held on 25/09/2015 at the Oda Hall on the university's main campus under the theme of "Pastoralism and climate change resilience?" organized by the Research Directorate and President's Office.

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ልማት ማዕከል ወቅቱን ጠብቆ ስንዴ መዝራት መጀመሩን ገለፀ፡፡

ሚያዚያ 12/2015 ዓ.ም 
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ልማት ማዕከል ወቅቱን ጠብቆ ስንዴ መዝራት መጀመሩን ገለፀ፡፡
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ልማት ማዕከል በ2015 ዓ.ም ምርት ዘመን በሰላሳ ሄክታር የእርሻ መሬት ላይ ምርጥ ዘርና ግብዓት በመጠቀም ስንዴ መዝራት መጀመሩን አሳዉቋል፡፡የግብርና ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት መ/ር ሀሮ አዱላ እንደገለፁት የተዘሩት የስንዴ ዓይነቶች "ቀቀባና ኪንግ በርድ" የሚባሉ መሆናቸዉን በመጠቀስ ይህም በሄክታር ከ33-35 ኩንታል ምርት ሊገኝ እንደምችል ተናግሯል፡፡
መ/ር ሀሮ አያይዘዉም የእርሻ ሥራዉ ለዩኒቨርሲቲዉ በገቢ ምንጭነት ከማገልገሉም በላይ ለመማር ማስተማር ፤ለምርምርና ለማህብረሰብ አገልግሎት ከፍተኛ ጥቅም ያለዉ መሆኑን በመግለጽ በቀጣይም በግብርና ልማት ማዕከል ሥር የተለያዩ የእርሻ ሥራዎችን በስፋት ለማከናወን እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ 
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በድርቅ ለተጎዱ  ለአካባቢው ማህበረሰብ 355 ኩንታል የስንዴ ምርጥ ዘር ማከፋፈሉን ገለፀ፡፡

ሚያዚያ 12/2015 ዓ.ም
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በድርቅ ለተጎዱ  ለአካባቢው ማህበረሰብ 355 ኩንታል የስንዴ ምርጥ ዘር ማከፋፈሉን ገለፀ፡፡
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በኦሮሚያ ህብረት ሥራ ኢንተርፕራይዝ የተዘጋጀውን  በመግዛት  የስንዴ ምርጥ ዘር  ማከፋፈሉን ገልፀዋል፡፡የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍቃዱ ወ/ማርያም የተገዛውን  የስንዴ ምርጥ ዘር ለምዕራብ ጉጂ ዞን ም/አስተዳዳሪ ርክክብ ባደረጉት ወቅት እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲዉ የልህቀት ማዕከል አደርጎ ከሚሰራባቸዉ ሥራዎች አንዱ የግብርና ልማትን ማስፋፋት መሆኑን በመጥቀስ ይህ እየተከፋፈለ ያለዉ የስንዴ ምርጥ ዘር በአምስቱ ወረዳ ዉስጥ ላሉና በይበልጥ  በድርቅ ጉዳት ለደረሰባቸዉ የህበረተሰብ ክፍል  መሆኑን ገልፀዉ በቀጣይም ዩኒቨርሲቲዉ ተመሳሳይ ሥራዎችን በማህብረሰብ አገልግሎት በኩል አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግሯል፡፡   

Pages