በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ አስተባባሪነት በቡሌ ሆራ ከተማ ለበሪሶ ዱካሌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሴት ተማሪዎች ሥልጠና ተሰጠ፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም (BHU)
የዩኒቨርሲቲዉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ በዩኒቨርሲቲዉ ያሉ ሴት ተማሪዎችን በተለያዩ መንገዶች ለማብቃት እየሠራ ካለዉ ሥራ በተጨማሪ በአካባቢዉ ያሉና በቀጣይ ወደ ዩኒቨርሲቲ
ይገባሉ ተብሎ የሚታመኑ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሴት ተማሪዎች ጭምር ከተለያዩ ፆታዊ ጥቃቶች እንዲሁም ከተላላፊ በሽታዎች ራሳቸዉን እንዲጠብቁ እገዛ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖ የተዘጋጀ ሥልጠና ስለመሆኑ በዕለቱ ተገልጾዋል፡፡

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የዕቅድ ዝግጅት፤ክትትል;ግምገማና ሪፖርት አቀራረብን በተመለከተ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም (BHU)
የአቅም ግንባታ ስልጠናዉ የተዘጋጀዉ በትምህርት ሚኒስቴርና በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የስትራቴጅክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ የጋራ ትብብር ሲሆን ሥልጠናው የተሠጠው ለኮሌጅ ዲኖች; ለዳይሬክተሮች; ለሥራ አስፈጻሚዎች; ለትምህርት ክፍሎችና ለአስተባባርሪዎች ነው።
የሥልጠናው ዋና ዓላማ በዕቅድ ዝግጅት፤ክትትል; ግምገማና ሪፖርት አቀራረብ ዙሪያ የሚስተዋለውን ክፍተትና የአቅም ውስንነት ችግሮችን በመቅረፍ የታዩትን ክፍተቶች ለመሙላት ታስቦ የተዘጋጀ ስለመሆኑ ተገልጿዋል።
በሥልጠናዉ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ ሲሆኑ የስልጠናዉን አስፈላጊነት በሚመለከት መሠረታዊና ቁልፍ መልዕክቶችን ለሠልጣኝ ባለሙያዎቹ አስተላልፏል፡፡

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የኢንጅነሪንግ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር ሴሚናር-ዎርክ ሾፕ አካሄደ፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 24/2017
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ኢንጅነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ የሚያከናዉናቸዉን ተግባራትን በተመለከተ የጋራ ዓላማና ቀጣይነትን ባረገገጠ መልኩ ማስከድ እንዲቻል በ2017 የት/ዘመን ኮሌጁ ለማከናወን ካቀዳቸዉ አምስት ወርክ ሾፖች መካከል የመጀመሪያ ዙር በዛሬዉ ዕለት በኮሌጁ ስር ከሚገኙ ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ከተወጣጡ መምህራን ጋር ተካሂዷል፡፡
በወርክ ሾፑ ላይ ተገኝቶ መልዕክት ያስተላለፉት የኢንጅነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ዲን መ/ር ቦሩ ቤደያ ሲሆኑ የወርክ ሾፑ ዋና ዓላማ በኮሌጁ ሥር ያሉ መምህራን የእርስ በርስ ልምድ ልዉዉጥ አድረገዉ የተሻለ ሥራ መሥራት እንዲችሉና በአሁኑ ሰዓትም እያንዳንዱ ትምህርት ክፍል የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ሥራዎቻቸዉን ከማከናወን አንጻር ያሉበትን ደረጃ ለመፈተሽ አጋዥ መድረክ ስለመሆኑ አንስቷል፡፡

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ በ2017 ዓ.ም ሊተገበሩ የሚገቡ ቁልፍ ዉጤት አመላካች ሥራዎችና ተግባራት ዙሪያ ከየዘርፉ ም/ፕሬዝዳንቶች ጋር የሥራ ዉል ተፈራረሙ፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 24/2017
በቅርቡ ትምህርት ሚኒስቴር ከአርባ ሰባት የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በ2017 የትምህርት ዘመን በሚተገበሩ ቁልፍ ዉጤት አመላካች ጉዳዮች ዙሪያ ከየፕሬዝዳንቶቻቸው ጋር የሥራ ዉል መፈራረሙ ይታወሳል፡፡
በዚሁ መሠረት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማም በቀን 23/04/2017 ዓ.ም ከአካዳሚክ ምርምር; ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህብረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት፤ከአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንትና እንዲሁም ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ጋር የአፈፃፀም ዉል የፊርማ ሥነ ሥርዓት አከናዉኗል፡፡

Pages