ኢንጅነሪንግ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ለላብራቶሪ ባለሙያዎች እና ለሁለተኛ ድግሪ ተማሪዎች በ‹‹ MATLAB››ሶፍት ዌር አጠቃቀም ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
Posted by admin on Friday, 17 January 2025ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም (BHU)
የዩኒቨርሲቲዉ ኢንጅነሪንግ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በስሩ ያሉትን የመምህራንና የባለሙያዎችን አቅም በተለያዩ አቅም ግንባታ ሥልጠናዎች ለማጎልበት የተለያዩ ስልቶችን ቀይሶ እየሰራ ይገኛል፡፡
በሥልጠናዉ ዕለት ተገኝቶ መልዕክት ያስተላለፉት የኢንጅነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ዲን መ/ር ቦሩ ቤደያ በኢንጅነሪንጉ ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት ተያያዥነት ያላቸዉ በመሆኑ ለመምህራን እየተሰጠ ካለዉ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በተጨማሪ ለላብራቶሪ ባለሙያዎች እና ለሁለተኛ ድግሪ ተማሪዎች መስጠቱ አስፈላጊ ሆኖ ስለታመነበት በ‹‹ MATLAB››ሶፍት ዌር አጠቃቀም ዙሪያ ሥልጠና መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡