የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት አባላት ከተማሪ ተወካዮች ጋራ የውይይት መድረክ አካሄዱ።
Posted by admin on Wednesday, 26 March 2025

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ,መጋቢት 13/2017 (BHU)
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕረዘዳት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ፣ የአካዳሚ ቴክ/ ሽግ/ማ/አ /ም/ፕ ዶ/ር ገበየሁ አሻግሬ ፣ የተማ/አስተዳደር ልማት ም/ፕረዘዳት ዶ/ር ነጌሳ መኮና እንዲሁም የአካዳሚ ጉዳዮች ዳ/ዳ ዶ/ር መኩሪያ ጉዬን ጨምሮ በመድረኩ ላይ በመገኘት የተማሪ ተወካዬችን በአጠቃላይ ስለ መማር ማስተማሩ ዙሪያ አነጋግረዋል።
በዉይይት መድረኩ ላይ አጠቃላይ በግቢዉ የሚሰጠዉን አገልግሎት፣ የመማር ማስተማር ሂደትን ፣ የካፌ ፣ የትራንስፖርት ፣ የቤተ-መፅሀፍት አገልግሎት እንዲሁም ለተመራቂ ተማሪዎች የመዉጫ ፈተና ዝግጅት ላይ ከተማሪ ተወካዮች ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን አመራሩም የቀረቡትን ችግሮች በመዉሰድ እና በፍጥነት መቀረፍ ያለበትን ጉዳይ ትኩረት በመስጠት እንደሚሰሩ በማስረዳት ምላሽ ሰተዋል።
በመጨረሻም ማንኛዉም የ2017 ዓ.ም የመዉጫ ፈተና የሚወስድ ተመራቂ ተማሪ የቢሔራዊ መታወቂያ ካርድ " National ID" ማዉጣት እንዳለበት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ አሳስበዋል።