የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በe-SHE ዙሪያ ለተማሪዎቹ ገለፃ አደረገ፡፡
Posted by admin on Wednesday, 6 November 2024
ጥቅምት 13/2017 ዓ.ም
በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የትምህርት አሰጣጥ ሁኔታን በኦንላይን ለመስጠት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለዉ ስለመሆኑ የተነገረለት e-SHE (e-learning for strengthening higher education) ባለፈው የትምህርት ዘመን የሬሜዲያል ትምህርታቸውን ተከታትለው በ2017 የትምህርት ዘመን ለአንደኛ ዓመት ለተመዘገቡ ተማሪዎችና ከ2ኛ ዓመት በላይ ላሉት መደበኛ ተማሪዎች በአይሲቲ ሥራ አስፈፃሚ በኩል ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
ገለፃዉን ያደረጉት የአይሲቲ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወንድማገኝ ሸበራ ሲሆኑ ኮርሱን ወስደው ለጨረሱ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት የሚሰጥ መሆኑንና በፈተናዉም ከ80% በላይ ማምጣት የሚጠበቅ ስለመሆኑም ተናግሯል፡፡