የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ተልዕኮ በአግባቡ እንዲወጡ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
Posted by admin on Tuesday, 18 March 2025

(መጋቢት 05/2017 ዓ.ም)
(መጋቢት 05/2017 ዓ.ም) በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የተዘጋጀው የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት ብቃት ማረጋገጫ ማስፈጸሚያ ሠነድ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሽኔ በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች በትግበራ ላይ መሆናቸውን አንስተዋል።
በዚህም የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት የሥርዓተ ትምህርት ለውጥና የመውጫ ፈተና እንዲሁም በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ብሄራዊ የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተግባራዊ በመደረግ ላይ መሆኑን አንስተዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ተልዕኮ በሚገባ እንዲወጡም በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ሚንስትር ዴኤታው ለውይይት የቀረበው የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት ብቃት ማረጋገጫ ማስፈጸሚያ ሠነድ ዝግጅትና ትግበራም የዚሁ አካል መሆኑን አስገንዝበዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኤባ ሜጄና በበኩላቸው ትምህርት ሚኒስቴር በአዋጅ የተሠጠውን ተልዕኮ ለማስፈጸም በርካታ ማሻሻያዎችን እያደረገ መሆኑን ያነሱ ሲሆን የተዘጋጀው የ3ኛ ዲግሪ ትምህርት ብቃት ማረጋገጫ ማስፈጸሚያ ሠነድ በየደረጃው ላሉ የስራ ሀላፊዎች፣ አሠልጣኞችና ሠልጣኞች ወጥ የሆነ አሠራር ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን አስገንዝበዋል።
በመድረኩም የተዘጋጀው የ3ኛ ዲግሪ ትምህርት ብቃት ማረጋገጫ ማስፈጸሚ ሠነድ ለዩኒቨርሲቲ ተወካዮች ቀርቦ ወይይት የተደረገበት ሲሆን በዝግጅት ሂደቱ ተሳትፎ ላደረጉ ምሁራን የእውቅና ሠርተፍኬት ተሠጥቷል።
ትምህርት ሚኒስቴር