በቡሌ ሆራ ማስተማሪያ ሆስፒታል አንድ ኪሎ ግራም የሚመዝን እጢ ከአንድ ታካሚ አንገት ላይ ተወግዷል።
Posted by admin on Friday, 17 November 2023
ህዳር 06/2016 ዓ.ም
ታካሚዋ ከአምስት አመት በላይ አንገቷ ላይ እጢ የነበረባት ሲሆን በሆስፒታሉ ውስጥ የተለያዩ ምርመራ እና ህክምና ከተደረገላት በኋላ እጢው ያለምንም ችግር ተወግዶላታል።
በቡሌ ሆራ መማሪያ ሆስፒታል ውስጥ በተለያዩ ህክምና ዘርፍ ላይ ስፔሻላይዝ ያደረጉ የቀዶ ህክምና ባለሙያዎች ስላሉ ህብረተሰቡ ይህንን ተረድቶ እንዲጠቀምበት የሆስፒታሉ ማኔጅመንት እስታውቋል::