የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በህክምናና በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸዉን ተማሪዎች አስመርቋል።

የካቲት 15/2017 ዓ.ም

ዩኒቨርሲቲዉ ለ13ኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸዉን የመጀሪያ ዲግሪ 398 እና በሁለተኛ ዲግሪ 236 በድምሩ 634 ተማሪዎች የተለያዩ ክብር እንግዶች በተገኙበት ያስመረቀ ሲሆን ተመራቂዎቹም በዋናነት በህክምና በሌሌች ትምህርት ዘርፎች የሰለጠኑ ስለመሆናቸዉ ተገልጾዋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱም ላይ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ ለተመራቂዎች ያላቸዉን መልካም ምኞት በመግለጽ በቀጣይ በሰለጠኑት ሙያ ለሀገራቸዉ ዕድገትና ስኬት ማበርከት ባለባቸዉ አስተዋጽኦ ዙሪያ ቁልፍ ንግግር አድርጓል።

ዶ/ር ብርሃኑ ለማ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ብቁና ተወዳዳሪ የተማረ ሰው ኃይል የማፍራት ተልዕኮዉን እየተወጣ መሆኑን በመግለጽ በአሁኑ ሰዓት ከ14 ሺህ በላይ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸዉ ላይ እንደሚገኙ አስረድቷል ።

አያይዘዉም ፕሬዝዳንቱ ዩኒቨርሲቲዉን ወደ ለቀ ደረጃ ለማድረስ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸዉን የገለጹ ሲሆን የትምህርት አሰጣጡም ጥራትና አግባብነት ባላቸዉ ፕሮግራሞች ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ ስለመሆኑ ጠቅሷል።

በመጨረሻም ፕሬዝዳንቱ ባስተላለፉት መልዕክት ተመራቂዎች በዩኒቨርሲቲው ቆይታ ወቅት በቀሰሙት ዕዉቀት መሠረት ጠንካራ ተወዳዳሪና ስራ ፈጣሪ ሆነዉ ሀገራቸዉን እንደሚለዉጡም ሙሉ እምነታቸዉን የገለጹ ሲሆኑ ለተመራቂዎች የዛሬዉ ቀን የወደፍት ህይወታቸዉ አንድ እርምጃና የማይረሳ ቀን ነው በማለት ከምረቃዉ በኃላም የዩኒቨርሲቲዉ ምርጥ አምባሳደሮች እንዲሆኑም ጠይቋል።