ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እና ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ
Posted by admin on Tuesday, 4 March 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እና ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት፤ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድማሱ ዳምጠው እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ብርሃኑ ለማ (ዶ/ር) ናቸው፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ሥራው በተጨማሪ፤ የማዕድን እና የቡና ምርት ዘርፍን ለማገዝ የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡
የገዳ ሥርዓትን ለማስተዋወቅ ሥርዓተ-ትምህርት ቀርጾ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ እያስተማረ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱም፤ ዩኒቨርሲቲው የሚያከናውናቸውን ተግባራት በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በኩል ለሕብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡