የGAT(Graduate Admission Test) ስልጠና ለመውሰድ ለተመዘገባችሁ በሙሉ፣

ቀን 15/2016 ዓም
ማስታወቂያ

ስልጠናው የሚሰጠዉ ሀምሌ 19 እና 20/2016 ዓ/ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት ስለሆነ ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በተጠቀሰዉ ቀን በግቢዉ በሚገኘዉ አባጡንጋ መታሰቢያ አዳራሽ በአካል ተገኝታችሁ ስልጠናውን እንድትከታተሉ እናሳዉቃለን።

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ የማስተማሪያ ሆስፒታል የዓይን ህሙማንን የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና አገልግሎት መሰጠት ተጀመረ።

ሀምሌ 08/2016 ዓ/ም

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ የማስተማሪያ ሆስፒታል፣የጤና ሳይንስ እንስቲትዩትና የህማሊያን ካታራክት ፕሮጀክት (HCP) (መንግታዊ ያልሆነ ድርጅት) ጋር ተባብሮ መስራት ከጀመረበት ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ እስካሁን ከአንድ ሺህ ሁለት መቶ በላይ የዓይን ህሙማንን የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና ያደረገ ሲሆን፣ ከዛሬ ሐምሌ 8-12/2016 ድረስ ለአምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የህክምና አገልግሎት ከአራት ዞኖች ለሚመጡ ከ600 በላይ ህሙማን የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና ለመስጠት ስራ መጀመራቸውን የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ እንስቲትዩት ቺፍ ኤክስኩዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ሳፋይ ኤለማ አስታውቀዋል ።

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዙር የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና አስጣጥና ስነ-ስረዓትን በተመለከተ ኦረንቴሽን ተሰጠ።

ሀምሌ 08/2016 ዓ/ም

በዩኒቨርሲቲዉ በሁለተኛ ዙር ፈተናዉን ለሚወስዱ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የፈተናዉን አሰጣጥና ስነ-ስረዓትን በተመለከተ በዩኒቨርሲቲዉ ቅጥር ግቢ ኦረንቴሽን የተሰጠ ሲሆን፣ ኦረንቴሽኑን የሰጡት የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ ሲሆኑ በተሰጠዉ ኦረንቴሽን ተማሪዎቹ በፈተናዉ ወቅት መከተልና ማክበር የሚገባቸዉን ህጎችና ስነ-ስረዓቶች በተክክል እንዲገነዘቡ ተደርጓል።

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና እንዲፈተኑ የተመደቡ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ መዕከሉ እየገቡ ይገኛሉ።

ሀምሌ 06/2016 ዓ/ም

በዩኒቨርሲቲዉ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና እንዲፈተኑ የተመደቡ ተማሪዎች ከዛሬ ሀምሌ 06/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 5;30 ጀምሮ ከዙሪያዉ ከሚገኙ ዞኖችና ወረዳዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ቅጥር ግቢ እየገቡ ሲሆን፣ በሁለተኛ ዙር ለፈተናዉ የሚቀመጡ ተማሪዎች ብዛት ወንድ 4624 ሴት 2200 በጥቅሉ 6824 ናቸዉ።  ለተማሪዎቹ በተደረገዉ የአቀባበል ስረዓት ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንቶችና የስራ አመራሮች ሲሆኑ አቀባበሉን በምርቃት የከፈቱት የአካባቢዉ አባገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ናቸዉ።

Pages