በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከምርምር ሥራ ጋር የተያያዘ ስልጠና
Posted by admin on Tuesday, 25 January 2022በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከምርምር ሥራ ጋር የተያያዘ ስልጠና
*******
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በፕሮፖዛል አዘገጃጀት፣ በፕሮጀክት አቀራረፅ እና ሌሎች ከምርምር ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
ሥልጠናው የተሰጠው ከተለያዩ የዩኒቨርሲቲው ኮሌጆችና እንሰቲቲዩቶች ለተውጣጡ መምህራኖች ሲሆን፤ ሥልጠናው ከጥር 14-17/2014 ዓ.ም ላለፉት ሦሥት ቀናት በተከታታይ ሲሰጥ ቆይቶ ነጌ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ሥልጠናው የተዘጋጀው በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕ/ጽ/ቤት ሲሆን፤ በዘርፉ ልምድና ዕውቀትን ያካበቱ ምሁራን ሥልጠናውን ለመምህራን ሲሰጡ ቆይተዋል።