በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና ተሰጠ፡፡
Posted by admin on Monday, 4 December 2023የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ዓመታት በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት HCP (Himalan Cataract Project ) ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመፈራረም ወደ ሥራ መግባቱ ይታወሳል፡፡
በመሆኑም በስምምነቱ መሠረት ለ2ኛ ዙር የድርጅቱ ተወካይ አቶ ሀገሩ ከበደ በተገኙበት ከ17/03/2016-21/03/2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ነፃ የአይን ሞራ ግርዶሾ ቀዶ ጥገና በሆስፒታሉ እየተሰጠ ይገኛል፡፡ የቀዶ ጥገና ዘመቻ ሥራዉን በሚመለከት ማብራሪያ የሰጡት በሆስፒታሉ የዓይን ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር አያኖ ባሳዝን ድርጅቱ "Cure blindness" የሚል መሪ ቃል ይዞ የሚሰራ መሆኑን በመግለጽ የዓይን ሞራ ግርዶሽ በአመዛኙ ሰዎች እድሜያቸዉ ከ55 በላይ ሲሆን የሚከሰት መሆኑን እና በተጨማርም በዓይን ላይ በሚደርስ አደጋ እና በሌሎች የዓይን በሽታዎች እንዲሁም አብሮ በመወለድ የሚመጣ መሆኑን ተናግረዋል፡፡