ማስታወቂያ
Posted by admin on Friday, 17 January 2025

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጥር 02/2017 ዓ.ም(BHU)
የመውጫ ፈተና ለምትጠባበቁ መምህራንና እጩ ተመራቂዎች በሙሉ::
በክረምት መርሓ ግብር በመምህርነት ሙያ ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ድግሪ የትምህርት እርከን ማሻሻያ ስልጠና ስትከታተሉ የቆያችሁና፤እንዲሁም በቅዳሜ እና እሁድ የትምህርት መርሓ ግብር ስትከታተሉ ቆይታችሁ የመውጫ ፈተናውን ያልወሰዳችሁ ሠልጣኞች፤የመውጫ ፈተና የሚሠጠው ከየካቲት 10-12/2017 ዓ.ም ስለሆነ ፈተናው የሚመለከታችሁ አካላት በሙሉ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ አጥብቀን እናሳውቃለን፡፡
የአካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት