ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ 'YeQaQe' ከተባለ ሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅት ጋር የሥራ ማስጀመሪያ ውይይት አካሄደ።
ካቲት 19/2018 ዓ.ም :ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
ዩኒቨርሲቲዉ 'YeQaQe' ከተባለ እና "New Years to Empower Women and Youth for resilient Citizen" በሚል ሀሳብ በተለየ መልኩ በኢኮኖሚዉ ዘርፍ የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሚሠራ ሀገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር ለመስራት ከዩኒቨርሲቲዉ የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላትና የድርጅቱ መስራች ወ/ሮ ሙላቱዋ እንዲሁም ከጀርመን ሀገር በድርጅቱ ጋባዥነት ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ከመጡት ፕሮፌሰር አደራጀዉ ዋካ በተገኙበት አጠቃላይ ዉይይት ተደርጎ ቀጣይ በጋራ በሚሠሩ ሥራዎች ዙሪያ አቅጣጨ ተቀምጧል፡፡
በመድረኩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲዉ አካዳሚክ፤ምርምር፤ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህብረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገበየሁ አሻግሬ በሰጡት ሀሳብ ዩኒቨርሲቲዉ በዋናነት በመማር ማስተማር፤በምርምና በማህብረሰብ አገልግሎት በኩል የተሰጣዉን ተልዕኮዎች ለማሳካት በመንግስት ብቻ በሚመደብ በጀት ማሳካት የማይቻል በመሆኑ ከሌሎች ሀገር በቀልና ከሀገር ዉጭ ካሉት መንግስታዊ ካልሁኑ ድርጅቶች ጋር በጥምረት መሥራቱ አስፈላጊ መሆኑን አስረድቷል፡፡
የዩኒቨርሲቲዉ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ በበኩላቸዉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልዕኮያቸዉን ለማሳካት መንግስትን መጠበቅ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ አማራጮችን መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዉ ፤ግለሰቦች ቢቀያየሩም ሥራዉ የሚሠራዉ ለትዉልድ በመሆኑ እና ይህም ልሳካ የሚችለዉ ሥራዉ በበይበልጥ በባለሙያዎች ከተመራ ነዉ በማለት ከገለጹ በኃላ አሁንም ባሉበት ሆነዉ ዩኒቨርሲቲዉን እየደገፉ መሆናቸዉን በመናገር በቀጣይም አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡
በዕለቱም በዩኒቨርሲቲዉና በግብረሰናይ ድርጅቱ መካከል የሥራ ስምምነት እንዲፈጠር ከፍተኛ ሚና የተጫወቱት የዩኒቨርሲቲዉ ምርምርና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መ/ር አንተነህ ፍቅሬ አጠቃላይ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ያለበትን ደረጃና የትኩረት መስኮች እንዲሁም ከአጋር ድርጅቱ ጋር በምን አግባብ መስራት እንደሚፈልጉ ገለፃ ካደረጉ በኃላ የጤናኢንስቲትዩት፤የምርምር ፤ስርፀት እና ስነ-ምግባር ዳሬክቶሬት እንዲሁም የማህብረሰብ ጉድኝትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት የሥራ ኃላፊዎች ከግብረሰና ድርጅቱ ጋር ለመስራት በሚፈልጉባቸዉ ጉዳዮችና ለስራዉም ስኬት ባሉ ምቹ ሁኔታዎች ዙሪያ ገለፃ አድረገዋል፡፡
በሌላ በኩል 'YeQaQe ፕሮጀክት' መሥራች ወ/ሮ ሙላቷ በበኩላቸዉ ድርጅቱ ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጋር ለመስራት በመብቃቱ እጅግ በጣም ደስተኛ መሆናቸዉን በመግለጽ ድርጅታቸዉ ቀደም ሲል ከተለያዩ መ/ቤቶች ጋር በጥምረት በመሥራት ዉጤት ያስመዘገባቸዉን ሥራዎች በመጥቀስ፤ድርጅቱ የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በከተማ ግብርና ዙሪያ የሚሠራ መሆኑን፤በአየር ንብረት ለዉጥ፤በጾታዊ ጥቃትና ጎጂ ባህሎች ዙሪያ እና የዲጂታል ጤና አገልግሎትን በገጠራማ የሀገርቷ አካባቢዎች ስለማዳረስና በመሳሰሉ ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰራ ድርጅት መሆኑን አስረድቷል፡፡
በተጨማሪ ከድርጅቱ ጋር በመሆን የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲን ለመደገፍ ከጀርመን ሀገር የመጡት ፕሮፌሰር አደራጀዉ ዋካ በበኩላቸዉ ባላቸዉ ሙያ በጤናዉ ዘርፍ ዩኒቨርሲቲዉን የመደገፍ ሥራ እንደሚሠሩ፤የተለያዩ አጋር ድርጅቶችን ከዩኒቨርሲቲዉ ጋር ትስስር እንዲፈጥሩና የህክምና መሣሪያዎችን ጭምር ድጋፍ እንዲያደርጉ በማገናኘት እንዲሁም ከበሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በየዓመቱ በግል ሁለት የጤና ተማሪዎችን የመደገፍ ሥራ እንደሚሠሩና ከአሁን በኃላም የዩኒቨርሲቲዉ አምባሳደር በመሆን በሄዱበት ሁሉ የማስተዋወቅ ሥራ እንደሚሠሩ በመድረኩ ላይ ገልጸዋል።




















































