በቡሌ-ሆራ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ህግና ስነ-ምግባር ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡
Posted by admin on Tuesday, 17 December 2024

በቡሌ-ሆራ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 18/2017 ዓ/ም (BHU)
ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ በምርምር ስነ-ምግባር ላይ ያተኮረ "Research Ethics and Scientific Integrity" በሚል ርዕስ የአቅም ግንባታ ስልጠና በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በመሰጠት ላይ ይገኛል።
በዩኒቨርሲቲዉ የጥናትና ምርምር ስራዎች በተለዩ የትኩረት መስኮች እነርሱም በማዕድን፣ በአገር-በቀል ዕዉቀቶች እና ግብርናን ማዕከል ያደረጉ የማህብረሰቡን ችግር በዘላቂነት የሚፈቱ ምርምሮች እየተተገበሩ ሲሆኑ፤ እስካሁን በተሰሩት ምርምሮች ላይ በስፋት ከታዩት ክፍተቶች መካከል አንዱ የምርምር ስነ-ምግባር ጉድለት ይጠቀሳል።
ስለሆነም ይሄን ክፍተት ለመሙላት ለተመራማሪዎች የምርምር ስነ-ምግባር እና ህግን አስመልክቶ ሥልጠና መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው ተመራማሪዎችም ይህንን ህግ ጠብቀው ምርምር ለማካሄድ ወይም ለማድረግ ይህ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደሚያግዛቸው ተመላክቷል።
ስልጠናውን ያዘጋጁት የምርምር ህትመት፣ ስነ-ምግባር እና ስርፀት ዳይሬክቶሬት ከት/ሚኒሲቴር ጋር በመተባበር ሲሆን ከሁሉም ኮሌጆች፣ ኢንስቲቱት እና ት/ቤት የተወጣጡ መምህራን ተሳትፈውበታል ።




















































