የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ በ2017 ዓ.ም ሊተገበሩ የሚገቡ ቁልፍ ዉጤት አመላካች ሥራዎችና ተግባራት ዙሪያ ከየዘርፉ ም/ፕሬዝዳንቶች ጋር የሥራ ዉል ተፈራረሙ፡፡
Posted by admin on Friday, 17 January 2025

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 24/2017
በቅርቡ ትምህርት ሚኒስቴር ከአርባ ሰባት የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በ2017 የትምህርት ዘመን በሚተገበሩ ቁልፍ ዉጤት አመላካች ጉዳዮች ዙሪያ ከየፕሬዝዳንቶቻቸው ጋር የሥራ ዉል መፈራረሙ ይታወሳል፡፡
በዚሁ መሠረት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማም በቀን 23/04/2017 ዓ.ም ከአካዳሚክ ምርምር; ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህብረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት፤ከአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንትና እንዲሁም ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ጋር የአፈፃፀም ዉል የፊርማ ሥነ ሥርዓት አከናዉኗል፡፡
ዶ/ር ብርሃኑ ለማ የአፈፃፀም ዉሉን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ቁልፍ ዉጤት አመላካች የሆኑ ነገሮችን በመለየት ለፈፃሚዎች ቆጥሮ በመስጠትና ቆጥሮ የመቀበል መርህን በተከተለ መልኩ መፈጸም እንዲቻል በተቋም ደረጃ ከቦርድና ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር መፈራረማቸዉን ገልፀዉ ይህንኑ ወደታችኛው የሥራ እርከን በማዉረድ ማስፈፀም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከዘርፎች ጋር የተደረገ የሥራ ግብ ስምምነት መሆኑን አስረድቷል፡፡
ዶ/ር ብርሃኑ በመጨረሻ በሰጡት የሥራ መመሪያ አሁን በዘርፍ ደረጃ የተከናወነዉ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት በአጭር ጊዜ ዉስጥ ወደ ታች እስከ ፈፃሚዎች ወርዶ ወይይት እንድደረግና ወደ ሥራ እንዲገባ ያሳሰቡ ሲሆን የድጋፍ፤የክትትል; የግምገማና የሪፖርት ሥርዓትም በሚመለከታቸዉ አካላት ትኩረት ተሰጥቶ እንዲከናወኑም አሳስቧል፡፡
በቁልፍ ውጤት አመላካች ጉዳዮች ዙሪያ ስምምነቱን የፈፀሙት የዩኒቨርሲቲዉ አካዳሚክ ምርምር; ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህብረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገበየሁ አሻግሬ ፤የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጌሳ ሞኮና እና የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መክታቸዉ ካሣዬ መሆናቸዉን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡




















































