በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ተቋርጦ የነበረዉ የተማሪዎች (One Card System) በድጋሚ ወደ ስራ ገባ።
Posted by admin on Saturday, 15 February 2025

(የካቲት 06/2017 ዓ/ም) ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
በዩኒቨርሲቲዉ ለተወሰነ ጊዜ ተቋርጠዉ የነበረዉ የተማሪዎች (One Card System) አገልግሎት በዛሬ ዕለት ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ መግባቱ የዩኒቨርሲቲዉ የአይሲቲ ( ICT) ስራ አስፈፃሚ አቶ ወንድምማገኝ ሸበራ አሳዉቀዋል፡፡
ስራ አስፈፃሚዉ እንደገለጹት የስስተሙ ዋና ዓላማ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ማሳለጥ፣የቁጥጥርና ክትትል ስርዓት ምቹ ማድረግ፣ የመመገብያ ካርድ ህትመት በማስቀረት የሃብት ብክነትን መቀነስ እና ፈጣን አገልግሎት ለተማሪ መስጠት ነዉ ብሏል፡፡
አክለዉም አቶ ወንድማገኝ እንገለጹት ተማሪ በአንድ ካርድ ብቻ ሁሉም አገልግሎት እንደሚያገኝና ከተፈቀደለት ካፍቴሪያ ዉጪ እና በተባለዉ ጊዜ ዉስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ መጠቀም እንደማይችል ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም በሚቀጥለዉ ምዕራፍ አገልግሎቱን ወደ ቤተ-መጻህፍትና የተማሪዎች ክሊኒክ እንደሚያስፋፉ ተናግሯል ፡፡




















































